እቃዎችን ቦታ መስጫ
እቃ አንድ ቦታ ማስቆም ይችላሉ ንድፎች ወይንም ክፈፎች በ ሰነድ ውስጥ: አንዴ አንድ ቦታ በማስቆሚያ ካስቀመጡት በ ቦታው ይቆያል ወይንም ማንቀሳቀስ ይችላሉ ሰነዱን ሲያሻሽሉ: የሚቀጥሉት ማስቆሚያ ምርጫዎች ዝግጁ ናቸው:
|
ማስቆሚያ |
ውጤት |
|
እንደ ባህሪ |
የ ተመረጠውን እቃ እንደ ባህሪ ማስቆሚያ በ አሁኑ ጽሁፍ ውስጥ: የ ተመረጠው እቃ እርዝመት አሁን ካለው ፊደል መጠን ከ በለጠ እቃውን የ ያዘው መስመር እርዝመት ይጨመራል በ HTML ገጽ ውስጥ ስእል መሀከል ለማድረግ: ምስሉን ያስገቡ እና አንድ ቦታ ላይ ያድርጉ "እንደ ባህሪ": እና ከዛ አንቀጹን መሀከል ያድርጉ |
|
ወደ ባህሪ |
የ ተመረጠውን እቃ ወደ ባህሪ ማስቆሚያ |
|
ወደ አንቀጽ |
የ ተመረጠውን እቃ ወደ አሁኑ አንቀጽ ማስቆሚያ |
|
ወደ ገጽ |
የ ተመረጠውን እቃ ወደ አሁኑ ገጽ ማስቆሚያ |
|
ወደ ክፈፍ |
የ ተመረጠውን እቃ በ ክፈፍ ዙሪያ ማስቆሚያ |
እቃ በሚያስገቡበት ጊዜ ንድፎች ወይንም ክፈፍ የ መልሕቅ ምልክት ይታያል እቃው ባለበት አካባቢ እቃውን በመጎተት ወደ ሌላ ቦታ ማንቀሳቀስ ይችላሉ የ እቃውን ማስቆሚያ ምርጫዎች ለ መቀየር በ ቀኝ-ይጫኑ እቃው ላይ እና ከዛ ይምረጡ ምርጫውን ከ ንዑስ ዝርዝር ውስጥ